Home » News (Page 50)
Category Archives: News
ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ የተላለፈ መዕልክት
ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ የተላለፈ መዕልክት
“ጌታ ሆይ ጸሎቴን ስማ
ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ
በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ ወዲያ አትመልስብኝ” መዝ. 102፡1-2
ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በተለያዩ የፖለቲካ ሥርዓቶች ውስጥ አልፋለች፤ በእነዚህም የፖለቲካ ሥርዓቶች ውስጥ ችግሮቻችንን በመወያየት በአብሮነት፣ በወንድማማችነት፣ የሁሉንም ዜጎች የጋራ ጥቅም ባከበረ መልኩ መፍታት ሳንችል ስለቀረን ጦርነትና ኃይልን ብቸኛ አማራጭ አድርገን በመውሰዳችን የብዙ ዜጎች ደም በከንቱ ፈሷል። ብዙዎች ለአካል ጉዳትና ለስነልቦና ቀውስ ተዳርገዋል፡፡ ብዙዎች ተሰደዋል፣ ለትውልድ ይተርፍ የነበረ ሐብትና ንብረት ወድሟል፡፡ ይህ በመሆኑ ምክንያት ሐዘን ሁሉም ቤት አንኳክቷል፡፡ ዛሬም እያንኳኳ ይገኛል፡፡
ባለፉት ቅርብ ዓመታት በትግራይ ምድር እንዲሁም በአማራ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በደቡብ፣ በሱማሌና በጋምቤላ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በተካሄዱት ጦርነቶችና ግጭቶች የፈሰሰው የዜጎች ደም ሁላችንንም ከልብ አሳዝኖናል አንገትም አስደፍቶናል። ውይይትንና መግባባትን ማስቀደም ባህላችን በማድረግ ፈንታ ወንድም በወንድም ላይ ሰይፍን በማንሳቱ ዜጎች ህይወታቸውን ሰቆቃ በተሞላ ሁኔታ እንዲኖሩ ሆኗል።
በያዝነው ሳምንት በትግራይ ምድር በተደረገው ጦርነት ህይወታቸውን ያጡ ወገኖች ለቤተሰቦቻቸው የማርዳት ሥራ እየተከናወነ ስለሆነ የብዙዎች ልብ በከፋ ሐዘን ከብዷል። ይህንን ሳምንት በሐዘን ወገኖቻችንን እንድናስብ የክልሉ መንግስት ማወጁን ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ጳጳሳት ጉባኤ የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን መግለጽ እንወዳለን። ልዑል እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ከቅዱሳንና ከጻድቃን ጋር ያኑርልን እንላለን። ቤተክርስቲያናችን ከሚያዝኑ ወገኖች ጋር ታዝናለች፣ ከሚያለቅሱትም ጋር ታለቅሳለች። ነገር ግን እንደጌታ ትእዛዝ ቤተክርስቲያን ሐዘኗም ለቅሶዋም ሙታንን ድል አድርጎ በተነሳው በክርስቶስ ባላት ተስፋ ላይ ሆና ነው፡፡ በድጋሚ እግዚአብሔር የሞቱ ልጆቻችንን ነፍስ በገነቱ ያሳርፋቸው፡፡ ውድ ልጆቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን። በተጨማሪም ልጆቻቸው መሞታቸውን ያልተረዱ ወላጆች እንዳሉ እናምናለን፡፡ ለእነርሱም ነፍስ ቤተክርስቲያናችን ትፀልያለች፡፡
አሁንም በአማራ ክልል እየተደረገ ባለው ጦርነት ስለሚሞቱ ሰዎች ቤተክርስቲያናችን ሐዘኗን ትገልጻለች። ስለእነርሱ ነፍስ በእግዚአብሔር ፊት ቀርባ ጸሎቷን ታቀርባለች። ዛሬም ካለፈው ስህተታችን እየተማርን ባለፈው ባጠፋነው እግዚአብሔር እንዲምረን ንስሐ እየገባን እርስ በእርሳችን በፍቅር በመወያየት ችግሮቻችንን ለመፍታት ይቅር እየተባባልን ጦርነትን በማስወገድና በፍቅር እንደ ወንድማማቾች አብሮ መኖርን ብቸኛ አማራጭ አድርገን እንድንይዝ ቤተክርስቲያን አጥብቃ ትማፀናለች። እግዚአብሔር አብሮ የመኖርን ጥበብ እንዲያድለን ትፀልያለች።
ጌታ ሆይ ለሞቱት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የዘላለም እረፍት ስጣቸው
የማያልቅ ብርሃን አብራላቸው
በሰላም አሳርፋቸው!
በሐዘን ለተጨነቁ ቤተሰቦችም መጽናናት ስጣቸው አሜን!
ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ
አዲስ አበባ
ጥቅም 6 ቀን 2ዐ16 ዓ.ም.
The Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia expressed condolences to those who lost their lives in the war in Tigray
CBCE strongly condemned all parties to prioritize the culture of dialogue and understanding and to stop causing misery in citizens
ADDIS ABABA, Ethiopia, October 21, 2023/APO Group/ –From October 16th – 18th, 2023, the Tigray regional government is informing families of those who lost their lives in the war in Tigray. It has been said that many are in deep grief of losing their dear ones and family members. Considering this the Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia (CBCE) (www.CBCE-gs.org) on October 17th, 2023, has released a message of condolences to families, all Ethiopians, and our Church in Tigray.
Our Church grieves with those who mourn, and cries with those who cry
The Message highlights that Ethiopia has gone through various political systems over the past years and through many of these times conflict has been experienced in diverse ways. Due to that many have lost their precious lives, and many were injured. Tigray, Amhara, Afar, Oromia, Benishangul Gumz, South, Somali, and Gambella are some of the primary areas where Ethiopia has experienced war and conflicts.
CBCE strongly condemned all parties to prioritize the culture of dialogue and understanding and to stop causing misery in citizens. The press release adds “Our Church grieves with those who mourn, and cries with those who cry. But according to the commandment of the Lord, the Church’s sorrow relies on her hope in Christ, who resurrected over death.”
Continuing the statement, the Bishops have asked to stop the ongoing war in the Amhara region and express the church’s sorrow for the people who are still dying. At the end, they call upon all individuals to learn from mistakes repent to God for what has been done in the past, and live only in fraternal spirituality.
Distributed by APO Group on behalf of the Catholic Bishops’ Conference of Ethiopia.