ዓዲግራት ሃገረ ስብከት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አጭር ታሪክ
ዓዲግራት ሃገረስብከት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በ1831 ዓ/ም በቅዱስ ኣቡነ ያዕቆብ ተመሰረተች። በዛን ግዜ ጥቅምት 19 ቀን 1832 ዓ/ም በአቢስንያ ሓዋርያዊ መስተዳድር (ፕሮፌክት ኣፓስቶሊክ) ሆነው ከተመሰረቱ አንድዋ ትግራይ ስትሆን እስከ አሁን እንሆ 179 ዓመት ሆኗታል። ከዛን ግዜ ጀምሮ ዓዲግራት ሃገረስብከት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የአቢስንያ ሓዋርያዊ መስተዳድር በመሆን ሓዋርያዊ አገልግሎት ስትፈፅም ብዙ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያና ማህበራዊ እንግልት፣ መከራ፣ ስደትና ጭንቀትን አስተናግዳለች። የኢትየጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሃገረ ስብከት ዓዲግራት በቅዱስ አባታችን ር/ሊቃነ ጳጳሳት 6ኛ መጋቢት 16 ቀን 1929 ዓ/ም ከሓዋርያዊ አስተዳደር አቢሲኒያ ተከፍሎ የትግራይ ሓዋርያዊ መስተዳደር የካቲት 1953 ዓ/ም ተቋቋመ። ከዘመን ወደ ዘመን መንፈሳዊ ጥንካሬዋን በማሳየት አሁን ወደ አለችበት የተረጋጋ ሕይወትና የማንነት ጥያቄዋን መልስ በማግኘት በማህበራዊና መንፈሳዊ እድገት በብቃት ለማረጋገጥ በቅታለች። በዓዲግራት ሃገረስብከት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሁለት ክልሎች (በትግራይና በአፋር) በእምነታቻው ፅኑ የሆኑ 24, 879 አከባቢ የሚሆኑ ምእመናንም ይገኙባታል። ብቃትና ጥራት ያላቸው መሪዎቿን በመያዝ መሰረቷን ሳትለቅ እስከ አሁን የእምነታችን መለያ የሆኑ ካህናትና ሴት መነኮሳት አልዋት።
የዓዲግራት ካቶሊካዊት ሃገረስብከት የዘርአ ክህነትና ዘመናዊ ትምህርት ቤት 1837-38 ዓ/ም በጐልዓ ኵድሓናይ ዓዲግራት እና ዓሊቴና እንደተጀመረ ይታወቃል። እንደዚሁም የዘርአ ክህነት አዳሪ ትምህርት ቤትም በዛን ዘመን እንደተጀመረ ታሪክ ያወሳል። ዓዲግራት ካቶሊካዊት ሃገረስብከት 33 ቁምስና እና 5 ቅድመ-ቁምስና (ቤተፀሎት) ያልዋት ሲሆን 6 ጳጳሳትና ብዛት ያላቸው የክርስቶስ አገልጋዮች ካህናትና ሴት መነኮሳትን ያፈራች ሃገረስብከት ናት። አሁን የሃገረስብከቱ ጳጳስ ብፁእ ኣቡነ ተ/ስላሴ መድህን ሲሆኑ፤ በሓዋርያዊ አገልግሎት ላይ የሚገኙ 87 ካህናት፣ ከብዛት ያላቸው መነኮሳትና ሴት ተማሪዎችን ያቀፈ 7 የተለያዩ የሴት መነኮሳት ገዳማት፣ እንደዚሁም ከመዋዕለ ህፃናት እስከ የፊሎዞፊና ትዮሎጂ ኮሌጅ 52 አብያተ ትምህርት ቤት፣ 8 የጤና ተቋም፣ 14 የስነ ማሳደጊያ ቤቶች፣ 4 ድኩማን መንከባከቢያና 7 የሴቶች ሙያ ማሰልጠኛ ማእከላት አልዋት። “…ልትሄዱና ልታፈሩ ሾምኋችሁ…” (ዮሓ.15:16)
የዓዲግራት ካቶሊካዊት ሃገረስብከት የሰው ልጆች ሁለንትናዊ እድገት በማምጣት መንፈሳዊና አካላዊ ብቃት እንዲኖራቸው ለሁሉም ዜጋ እኩል በሆነ አመለካከት ያለ ምንም አድልዎ የፆታ፣ የእድሜ፣ የሃይማኖት የዘርና የቀለም ልዩነት ሳታደርግ ከነበሩበት ወዳልነበሩበት የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ የዓዲግራት ሃገረስብከት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ፅሕፈት ቤት ሁለት ቅዱስ ዓላማ ይዞ በ1980 ዓ/ም ተመሰረተ። ይህ ባለ ሁለት ክንፍ ማብቅያ፦
• ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ቢሮ
• ማህበራዊ የልማት ማስተባበሪያ ቢሮ ይባላል።
‘ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ’ ሰዎችን መንፈሳዊ ትምህርትን እያስተማረ በስጋና በነፍስ ጥንካሬ ያላቸው ዜጋን ማፍራት ሲሆን ‘ማህበራዊ ልማት’ ደግሞ ከመንግስት ጐን በመሆን አንዳንድ መንግስት ያልደረሰባቸውን ቦታ በመድረስ ትምህርትና ህክምና ለማያገኙ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉትን ሕብረተሰብ በመዳሰስ ሁለንትናዊ ለውጥ እንዲያመጡ ማገዝ ነው።
ይህ እንዲህ እንዳለ፣ ለዚህ ሁሉ የለውጥ ሂደት የዓዲግራት ካቶሊካዊት ሃገረስብከት የመጀመሪያ ጳጳስ ብፁእ ኣቡነ ሃ/ማርያም ካሕሳይ የነበሩ ሲሆኑ የእድገቱም የለውጡም መነሻ የሆነ በዓዲግራት መንበረ ጳጳስ የሆነ ካቴድራል አለን። ይህን ያማረና የተዋበ ህንፃ ካቴድራል መድሃኔ ዓለም ቤተክርስትያን 1961 ዓ/ም ታንፆ ሲባረክ በዛን ግዜ የትግራይ መስተዳድር የነበሩ ልዑል መንገሻ ስዩም የነበሩ ሲሆን የዚህ ውብ ህንፃ ለመጎብኝት ሃፄ ሃ/ስላሴ ዓዲግራት ድረስ በመምጣት በካቴድራሉ ማማር በጣም እንደተደነቁ የእድሜ ባለፀጋዎች ተርከውልናል፡፡ ዓመት አልፎ አመት ይተካልና፤ ከውስጥና ውጭና ሃገር፣ ከመቂ ብፁእ አቡነ አብርሃም ደስታ ፣የኢትዮጵያ ካቶሊክ ፅሕፈት ቤት ሓላፊ ክቡር አባ ሓጐስ ሓይሽ ከነአጋሮቻቸው፣ከኤርትራ ብፁእ ጳጳስ አቡነ ፍቅረማርያም ሓጐስ ካህናት፣ ሴት መነኮሳት፣ ወጣቶችና ምእመናን ይዘው በመምጣት፤ እንደዚሁም የስራ አጋሮቻችን በመንግስት በሓላፈነት ደረጃ የተቀመጡ አመራሮች፣ ከተለያዩ ሃይማኖታዊ ተቋማት፣ በዓዲግራት ከተማ ከሚገኙ ማሕበረሰብ ጋር በመሆን እንሆ የቤተክርስቲያናችን ህንፃ 50ኛ ወርቃዊ ኢዮቤልዩ ለማክበር በቅተናል። “እናንተ ምሰክሮቼ ናችሁ” (ሉቃ. 24:48)
You must log in to post a comment.