IRROB.ORG

ፈጣሪ ሲረሳ

ሰው ፈጣሪውን በፍጹም ረስቶ፣
ከፍቅሩም መንገድ ጨሪሶ ወጥቶ፣
በፈጣሪ ቦታም ሀገርን ተክቶ፣
ኢትዮጵያዊው ኢትዮጵያውነቱን አጥፍቶ፣
ጥላቻውን ሲያስተጋባና ሲያሳይ በሚዲያ ዘርግቶ፣
ከፈሪሐ እግዚአብሔር የማሄድ ከቶ፤
ይልቅስ ወገንን ከማፋጀት ወደ አገር ገብቶ፣
የዘርነትና ጐሳነት ጥላቻን ሁሉ ትቶ፣
እርስበርስ ተዋደዱ በሚል በአምላክ ሕግ ተመርቶ፣
ፈጣሪ በሚሰጠው ረድኤትና ጸጋ ተመክቶ፣
ብሔራዊ ዕርቅና ሰላምን አብሮ መሥርቶ፣
መኖር ይሻላል የወገን ደምን ማፍሰስ ቀርቶ።

%d bloggers like this: