IRROB.ORG

Home » የአባ ተስፋማርያም አስታየቶች » የይቅርታ መንፈስ

የይቅርታ መንፈስ

ክርስቶስ በአማን ከሙታን ተነሳ፣
እንደ ኃያሉ የአራዊት-ንጉሡ አንበሳ፣
በጠላታችን በሰይጣን ላይ እያገሳ፣
ተሰቀለ ሞተ ተቀበረም ለኃጢአት ድምሰሳ፤
ሁሉን ፈወሰ ሳይቀር አንድም አንካሳ፣
ወደ አባቱ ጸለየ ሁሉን እንዲረሳ፣ 
ይቅር እንዲልም የጠላቶቹንም አበሳ፣
ሳያነሳባቸው የክፋታቸውን ወቀሳ፣
ለግፋቸውም ሳይጠይቅ አንዳችን ካሳ፣
መንግሥተ ሰማይን እንዲገቡ በደላቸውን ሳያወሳ፣
ተረስተው እንዳይቀሩ ከመሬት እንደገባ ሬሳ፣
አደራ እንዳይቀሩ አለ በየቀኑ ከሰማያዊው ምሳ።

%d bloggers like this: