IRROB.ORG

Home » የአባ ተስፋማርያም አስታየቶች » እንዳትገባ ወደ ፈተና

እንዳትገባ ወደ ፈተና

   

 

  

    

free counters

እንዳትገባ ወደ ፈተና፣
እንዳታጣም የመንፈስን ጤና፣
ቀጥ ብለህ ሂድ በአምላክ ጐደና፣
እንዳይጠፋብህ የብርሃኑ ፋና፣
አምላክ ፍቅር ብቻ ነውና፣
ወደ እርሱ ተመለስ ሳይመሽ ገና፣
አለበለዚያ ሰው ከተዘፈቀ በሙስና፣
በባሕር እንደሰጠሙ ሳይችሉ ዋና፣
ጠልቆ የቀሩት ሳይደርሱ ሲና፣
ተርበው የሞቱ ሳይበሉ ከመና፣
እንደዚህ ነበር እና የፈርዖናውያን ዜና።


እንዳትወድቅ ወደ ባሰው ትልቁ ፈተና፣
ወደ አምላክህ ተመለስ ጊዜ ሳለህ ገና፣
ሙሴ ሲዘገይ በተራራው ሲና፣
ምንም እንኳ አምላክ ቢያወርድላቸውም መና፣
ትዕግስትን አጥተው ክፉ ኃጢአትን  ሠርቷል እና፣
ከእስራኤላውያኑ ስማ የአወዳደቃቸውን ዜና፤
አንተም እንዳታጣ የመንፈስን ጤና፣
በባሕሩ እንደሰጠሙት ግብጻውያን ሳይችሉ ዋና፣
ሲሮጡ ሲሮጡ ሕዝቡን ለማሰቃየት በጭቈናና ጫና፣
በባሕር ተቀብረው የቀሩት እንደገና ከማየት የብርሃንን ፋና።


ሰው ተፈትኖ ከወደቀ፣
በኃጢአቱና ድካምነቱ እየተመጻደቀ፣
በአእምሮውም እየተራቀቀ፣
እየመሰለው ሁሉን የላቀ፣
ይኖራል ከፈጣሪ እንደራቀ፣
ከትቢተኛው ሰይጣን እየቦረቀ፣
በትዕቢትና ኃጢአት ህይወቱን የሰረቀ።

 

 

 

 

 

 

The 2 Week Diet

The 2 Week Diet

%d bloggers like this: