የአባ ተስፋማርያም ባራኪ አስተያየቶች
የሚመካ በእግዚአብሔር ብቻ ይመካ፤
ሰው በትዕቢት መንፈሱ ካልተነካ፣
ካልታወረም በቀር በጥላቻ ፖለቲካ፣
ይወቅ የፈጣሪ ችሎታና ጥበብ እንደማይለካ፤
ለሰው ነውና ሁልጊዜ ጥላ እንደ ትልቅ ወርካ፣
ፍቅሩም እንደወይን ጠጅ በውስጥህ የሚቦካ።
Advertisements