IRROB.ORG

Home » የአባ ተስፋማርያም አስታየቶች » ስለ ፍቅር » ፍቅር በፍጹም መስተንክር

ፍቅር በፍጹም መስተንክር

   

 

  

    

free counters

ፍቅር ነው በፍጹም መስተንክር፣
ሰው ከአውሬው አንበሳና ነብር፣
ሳይፈራ ተኝቶ አብሮ ያድር፣
ኃይል ነው ሁሉን የሚያስር፤
እራሱ አምላክ ፈጣሪ ነው ፍቅር፤
ሁሉን በዕውቀቱ በመፍጠር፣
በቼርነቱና ችሎታው የሚያስተዳድር፤
ማንም ፍጡር በዓለማችን እንዳይቸገር፣
ሕይውትን የሚሰጥ የእስትንፋስ አየር፣
ለሁሉ ፍጥረት ይሰጣል ስለሆነ ቼር፤
ሁሉም በደስታና ሰላም እንዲኖር፣
ያዛል ሁሉ ሰው እስርበርስ እንዲፋቀር፣
እንዲኖርም በዚህ ዓለም በመከባበር፣
ሳይለያይ በመልካም ሥራው በመተባበር።

 

 

 

 

 

 

 

%d bloggers like this: