የአባ ተስፋማርያም ባራኪ አስተያየቶች
ስማኝ ውድ ወገኔ፣
እንደማምነው እኔ፣
በሰው ላይ ጭካኔ፣
ከአምላክ ያመጣል ኵነኔ፣
ኋላም ያሰኛል ወይእኔ።
ጭካኔ በሰው ላይ መፈጸም፣
ከሰማይ ያወርዳል መርገም፣
ያስቀጣልም ከፈጣሪ ለዘላለም።
አንድ ሰው በሰው ላይ ከጨከነ፣
ሰውም በሰው ላይ ከወገነ፣
በአምላክ ፊት በደለኛ ስለሆነ፣
ፈጣሪንም በጣም ስለአሳዛነ፣
ይወቅ እራሱን እንደኰነነ፤
ከበጐ ሥራ ሁሉ እየቦዘነ፣
ክፋቱ በዓለም ላይ ስለገነነ፣
ስሙ ይጠፋል በንፋስ እንደበነነ፣
በራሱ ፈቃድ ሁሉን ስለወሰነ፣
ጥፋትንም እራሱ ላይ ስለበየነ፣
ሕይወቱን በከንቱ አባከነ።
Ethiopian Security Forces Filmed Extrajudicially Killing People Again
BREAKING: #Ethiopian security forces have again filmed themselves executing an individual who was tied to a tree. They continue to violate human rights due to the widespread impunity and non-accountability. pic.twitter.com/yBPy8tWT2t
— Yonas Nigussie (@Yonigussie) March 14, 2022
Advertisements