Advertisements
IRROB.ORG

Home » የአባ ተስፋማርያም አስታየቶች » ለአምላክ ይገበዋል ምስጋና

ለአምላክ ይገበዋል ምስጋና

ለአምላካችን ይገበዋል ታላቅ ምስጋና፣

ሁሉን የፈጠረ እርሱ ነውና፤
ሰውንም የሚመግብ በኅብስተ መና፣
ለዕፀዋት ዝናምን የሚያዘንም ከደመና፣
ይዘመርለት በመዝሙርና በጌና፤
የሚሰጠን ሁሉ ይሆነን ዘንድ ለጤና፣
እህሉ ያ ጣፋጭ ፍራፍሬውና ባናና፤
ሰውንም እንስሳትንም እኩል ይመግባልና፣
አዘውትረን እንለምነው ሁልጊዜ ይሰጠን ዘንድ እንደገና፤
የፍቅርና ሰላም ጸጋንም እንዲያፈስልን እንደ ባሕረ ጣና፣
ኢትዮጵያንም እንዲጠብቅልን ከእስግብግብነትና ሙስና፣
ይኸው ነውና ዛሬ በብዛት በሀገራችን የሚሰማው ዜና።

 

Advertisements

%d bloggers like this: